Monday, March 14, 2011

ስለ "ማኅበረ ቅዱሳን"

"ማኅበረ ቅዱሳን" የሚታዘዘው ለማን ነው?
ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ ሁኔታና የወደፊት ጣ የሚነጋገር ሁሉ የሚስማማበት አንድ ነገር አለ። ይኸውም "ማኅበረ ቅዱሳን" የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በአንድም በሌላም መንገድ በመከፋፈል እራሱን ብቸኛ የቤተ ክርስቲያንዋ ነጻ አውጪ አድርጎ የመመልከቱ ነገር ነው። አንዳንድ ጊዜማ ከማኅበሩ መመሥረት በፊት በቤተ ክርስቲያን ሥራ እንዳልተሠራ፣ እንዳልተደከመባት አድርጎ በድፍረት በመናገር የወጣቱን ክፍል ለማሞኘት ይሞከራል።  
ይህ ማኅበር ፊት የማያሳዩትን በስደት ውጪ ሀገር የሚኖሩትን አባቶች በማቃለልና ሃይማኖት ለዋጮች እንደሆኑ አስመስሎ በማቅረብ ለብዙ ክብር የበቁትን እያንዳንዳቸው ለቤተ ክርስቲያን ከሃምሳ ዓመታት በላይ የደከሙትን አባቶች በመናቅና በማዋረድ ወጣቶች ለአባቶቻቸው አክብሮት እንዳይኖራቸው ሰድቦ በማሰደብ በስደት ባሉባቸው ቦታዎች ሲያሳድዳቸው ተስተውሏል አሁንም እየተስተዋለ ነው። በቅዱሳን ስም ራሱን ለሚጠራ ማኅበር የከበሩትን ማዋረዱ የተመረጡትን መናቁ ስሙ እንደማይገባው የሚያሳይ ነው።
ይህ ብቻ አይደለም። ይኸው ማኅበር በስደት ያለችውን ቤተ ክርስቲያን ሲያሳድድ “ከአዲስ አበባ ሲኖዶስ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ መምሪያ ሥር የምተዳደር ነኝ” … “ሲኖዶስ አንዲት ናት” … “ከእናት ቤተ ክርስቲያን ጋር መደባለቅ ያስፈልጋል” በማለት በውጪ ያለውን ሕዝብ በመደለል ነው። ሙከራው እንዳሰበው ባይሳካለትም በቂ ጥፋት ለማጥፋት ያገኘውን አጋጣሚ ሁሉ ተጠቅሟል።
ማኅበሩ እራሱን በአዲስ አበባ ሲኖዶስ ሥር እንደሆነ አድርጎ ቢያቀርብም በምግባሩ ግን እዚያም ያሉትን አባቶች መከፋፈሉና አልታዘዝ ባይነቱ ዓይን እያወጣ ከመጣ ቆይቷል። እስከ አሁን አንዳንዶች በጠቅላይ ቤተ ክህነት የሚገኙ መምሪያ ላፊዎችን አንዳንድ አባቶችን በገንዘብ፣ ሌሎችንም ደካማ ጎናቸውን አሰመልክቶ ምስጢር እንደሚያወጣ በማስፈራራት አፋቸውን ለጉሞ ቆይቷል። የወደፊቱን እግዚአብሔር ያውቃል። እንደሚታወቀው ይህ ማኅበር “አጥፍተሃል” … “ተሳስተሃል” ... “አሁንስ በቃ! ... አልበዛም እንዴ?” የሚለውን ሁሉ “ተሐድሶ ናቸው” በማለት ወይም “ኑፋቄ አስተምረዋል” ብሎ ስም በማጥፋትና አመጽን በማስተባበር ቅን የቤተ ክርስቲያንዋን አገልጋዮች ስም እያጎደፈ ነው። ብዙዎች ጭንቅ ሆኖባቸው የማኅበሩን ድክመት እያወቁ ተሸክመው ባልተማሩ ልጆች እየታዘዙ “ስቀሉ ሲባሉ እየሰቀሉ” “አውርዱ ሲባሉ እያወረዱ” ማኅበሩ ሊያገኝ ከሚገባው በላይ ሥልጣን እንዲኖረው ምክንያት ሆነዋል። 
ያም ሆነ ይህ “ይህቺ ባቄላ ያደረች እንደሆነ አትቆረጠምም” እንደተባለው ወይም “ቁጭ ብለው የሰቀሉትን ቆመን ማውረድ እንዳያቅተን” ተብሎ እንደተተነበየው ዓይነት ነገር እንዳይመጣ ሁሉም ሊያስተውል ይገባዋል።
የወቅቱ የቤተ ክርስቲያን ችግር ማለትም የአባቶች መለያየትን ማኅበሩ የጥፋት ተልእኮውን ለመፈም ተጠቅሞበታል እየተጠቀመበትም ነው::  እንዲያውም ሁለቱንም ሲኖዶሶች በማቃለልና ባለመታዘዝ የማኅበሩን አጀንዳ የሚያካሂዱ ጥቂት አባቶችን እያታለለ ራሱን እንደ ሦሰተኛ አማራጭ እያቀረበ ነው:: ለዚህም ነው በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል ሰላም እንዲወርድ የማይፈልገው የተጀመረውን የሰላም የእርቅ እንቅስቃሴ ለማምከን የሚንቀሳቀሰው። በአባቶች መካከል ሰላምና እርቅ መምጣቱ ለቤተ ክርስቲያን የሚበጅ ሆኖ ሳለ በቤተ ክርስቲያን ሥር ነኝ ለሚለው ለ"ማኅበረ ቅዱሳን" አልዋጥ ማለቱ ማኅበሩ ድብቅና መተልእኮ እንዳለው በግልጽ የሚያሳይ ነው::       

ስለዚህ ማኅበር ጉዳይ ብዙ ማለት ይቻላል። የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ግን ከዚህ በታች ያለውን ደብዳቤ ለአንባቢ ለማቅረብ ሲባል እንደ መግቢያ እንዲሆን ብቻ ስለሆነ እዚህ ላይ እናበቃለን። እንደ ማጠቃለያ የምንለው ቢኖር ሁሉም አቅሙንና ደረጃውን ቢያውቅ፣ ሁሉም ድርሻውን እየታዘዘ ቢሠራ፣ ልጆችም ለመረገም በመቸኮል ፈንታ እንደ ልጅነታቸው በአባቶቻቸው እግር ሥር ቁጭ ብለው ተምረው ቢመረቁ እድሜያቸውም የሚረዝም ለቤተ ክርስቲያንም የሚበጅ መሆኑን ነው።

መልካም ንባብ … 


 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 



































 

3 comments:

  1. በጣም ይገርማል ፣ በርግጥም ማኅበረ ቅዱሳን እውነተኛ የቅዱሳን ማኅበር ቢሆን ኖሮ በቤተ ክርስቲያን እና በእውነቶኞቹ የዘመናችን ሐዋርያት ላይ መርዝን ባልረጨም ነበር ። ደግሞስ በቤተ ክርስቲያን ስር ነኝ እያለ ህገ ወጥ ስራን ከመስራት የተደበቀና የተሸፋፈነ አላማና ምግባር ከሌለው ለምን በሩን ከፍቶ ቤተ ክርስቲያን የምታዘውን አያደርግም? ማኅነሩ ያለውን የገንዘብ ልክ ማሳወቅ ፣ ኦዲት እንዲደረግ ሲመየቅ ፈቃደኛ መሆን ሲገባው ፣ ለምን ስራው ፣ ዓላማውና ዕቅዱ ድብቅ ሆነ? አቡነ ጳውሊስስ እውነተኛ የቢተ ክርስቲያን የበላይ አባት ከሆኑ ለምን በማኅበሩ ላይ እስካሁን እርምጃ አልወሰዱም? የጻፉትንስ ደብዳቤ ማነው በስራ ላይ የሚያውለው? ትዝ ሲላቸው ብቻ ደብዳቤ እያጻፉ ሲበትኑ ይህ የመጀመሪያ ጊዚያቸው አይደለም ፤ ከደብዳቤው በስተ ጀርባ ምን አይነት መልዕክት ነው ያለው?

    ReplyDelete
  2. AwdeSelam,
    Thank you for the information you share with us here.

    As I read the letter from the office of Aba Paulos, I was wondering what is behind it .... Can an organization that claims to be within the Church structure can be so independent? What initiated that? Is it may be it is difficult to work within the structure because of many disfunctional elements in the Church? May be.

    At the same time, the introduction seems to shade light on the intent of Mahibere Kidusan. I know few members who are very devouted to their faith. If I would see one weakness in them is that they have more dedication to Mahbere Kidusan that they have for the Church. I have seen them what they were capable of doing in Dallas, where I live, because Mahbere Kidusan could not its way in the local church.

    It is great to know that we are not the only ones who is having difficulty dealing with the Mahber.

    May the Lord show guide them the right path ....

    ReplyDelete
  3. This will bring mk's hidden agenda in to light. mk financial has not been accounted ye>. All the moneys collected by the mk in the name the church will belongs to the church. The church has full rights to be audit MK I don't understand why mk is afraid of auditing

    ReplyDelete