Sunday, January 9, 2011

ሰበር ዜና - ከቤተ ክርስቲያን የሰላምና የአንድነት ኮሚቴ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና የአንድነት ኮሚቴ በሜሪላን ከተማ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ አድርጎት በነበረው ስብሰባ ለመጪው የሰላምና የእርቅ ውይይት አስፈላጊ በሆኑ ቅድመ ዝግጅቶች ላይ እንደሚወያይና ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ ተጠብቆ ነበር። በዚህም መሠረት የደረሰን ዘገባ እንደሚያመለክተው የእርቅ ውይይቱን ስፍራ እና ጊዜ በተመለከተ ኮሚቴው ጥልቅ ውይይት ካደረገ በኋላ ስብሰባው በአሜሪካን ሀገር ከዐብይ ጾም መግቢያ በፊት እንዲሆን ወስኗል።  ባለፈው ዓመት ተደርጎ በነበረው የእርቅ ስብሰባ ዙሪያ የታዩትን ችግሮችን ለማስወገድ ይቻል ዘንድ ኮሚቴው የስብሰባውን ከተማና ቦታ እንዲሁም የስበሰባውን ጊዜ በዝርዝር እንደማይገለጽ ለመረዳት ችለናል። በአባቶች ስብሰባ ጊዜ ግራ አጋቢና ሃሳብ ከፋፋይ ግለሰቦች ድርሻ እንዳይኖራቸው አስፈላጊው ሁሉ ጥረት እንደሚደረግም የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።
ከዚህ ጋር አያይዞ የደረሰን ዜና እንደሚያመለክተው የእርቁን ስበሰባ በሚገባ ለማካሄድ ያመች ዘንድ ወጪውን ለመሸፈኛ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች በተለያዩ ከተማዎች ይደረጋሉ። ከዚህ ቀደም ተደርጎ ለነበረው ስብሰባ አስፈላጊው ወጪ በሰላምና አንድነት ጉባኤው አባላትና በጥቂት የቤተ ክርስቲያን ወዳጆች የተሸፈነ ቢሆንም ይህ ኃላፊነት የጥቂቶች ብቻ ሳይሆን የቤተ ክርስቲያንን ሰላም ለማየት የሚፈልጉ ሁሉ የጋራ ድርሻ እንደሆነ ጥርጥር የለውም። ከሥራቸው ፈቃድ በመውሰድ ለስብሰባ ዝግጅት አስፈላጊውን ጊዜ ከመሰዋት ባሻገር ብዙዎቹ የኮሚቴ አባላት የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ ለማገናኘት የሚያስፈልገውን ወጪ ከኪሳቸው አውጥተው ለመሸፈን እንደሚቸገሩ ለሁላችንም ግልጽ ነው ለመረዳት ችለናል። በመሆኑ እያንዳንዱ ምእመን ለዚህ ታሪካዊና መንፈሳዊ የእርቅና የሰላም እንቅስቃሰየ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ኮሚቴው ጥሪውን አስተላልፏል።  
ከዚህ በታች ያለው የኮሚቴው ደብዳቤ አስፈላጊውን መረጃ እንደሚሰጣችሁ እምነታችን ነው።

 

4 comments:

  1. ሰላም እግዚ አብሔር ከናንተ ጋር ይሁን።
    በቤተክርስቲያንያን አባቶች መካከል ለ፳ ዓመታት የፈጀውን መከፋፈል ወደ አንድነት ለማምጣት የምታደርጉት ጥረት በመርህ ደረጃ የሚደገፍ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም። ነገር ግን የክፍፍሉ ምክንያት የሆነው ፓትርያርክ በህይዎት እያለ ሌላ በመንበሩ ላይ ሊሾም አይገባውም የሚለው የቀኖና ሕግ ተጣሰ ተብሎ ነው። ታዲያ ኣሁን በፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደሕጋዊ መንበረ ሥልጣናችው ሊመለሱ ነው ? ወይስ ሕጉ እንደተጣሰ ስደተኛው ሕጋዊው የቤተክርስቲያን አባት በሕገ ወጡ አባ ጳውሎስ ሥር ሁነው የቀረውን የሕይወት ዘመናቸቸውን ሊያሳልፉ ነው ማለት ነው? በዚህ ሁኔታ ነው ያለውን ችግር ለመፍታት የምትሞክሩት?ለመሆኑ በስደተኞቹ ምዕመናን ሲገነቡ የቆዩት አብያተ ክርስቲያናት ባሰደዳቸው ሥራት ሊወረሱ ነው ማለት ነው ? አባ ጳውሎስ ከእገዛዙ ጋር ሰምና ወርቅ መሆናቸውን የማያውቅ ኢትዮጵያዊ ይኖር ይሆን?

    ReplyDelete
  2. Keep up this great work!

    ReplyDelete
  3. Dillu!

    The 1st we have to do as an ethiopian orthodox is bring all the father to the table, then go from there with prayer. We don't have to be afraid of discussion and reconcilation.

    ReplyDelete
  4. ድሉ አርፈህ ጸልይ።ሌላ ዓመት መጨመር አንፈልግም።ነው ሰላሙን አትፈልገውም?

    ReplyDelete